ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ያላጠናቀቁ 11 ሺህ 581 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስፈተን መጀመሩን አስታወቀ

2 Mons Ago
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ያላጠናቀቁ 11 ሺህ 581 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስፈተን መጀመሩን አስታወቀ

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ካሳሁን ተገኘ፤ ባለፈው ጊዜ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር የኒቨርሲቲው ሲሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ተቋርጦ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ተቋርጦ የነበረውን ፈተና ለመስጠት ተገቢው ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ጠቅሰው፤ ፈተናው ዛሬ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ የኬሚስትሪ ፈተና በመስጠት መጀመሩን ገልጸዋል።

በዛሬ ከሰዓት ክፍለ ጊዜ የባዮሎጂ፤ ነገ ደግሞ የስነ ዜጋ ትምህርት በመስጠት የፈተና ሂደቱ እንደሚጠናቀቅ ዶክተር ካሳሁን ተናግረዋል።

የፈተና ሂደቱ ሰላማዊ መሆኑን እና ተማሪዎች ፈተናውን በተረጋጋ መንፈስ እየወሰዱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎቹ ከጎንደር ከተማ እንዲሁም ከማዕከላዊና ከምዕራብ ጎንደር ዞኖች የመጡ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top