አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

1 Yr Ago
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢልዋል ቡቶ ዛዲሪ ጋር በካራቺ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ለማሻሻል ቁርጠኛ መሆኗን አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናግረዋል።

ግንኙነታቸው በተለያዩ የትብብር ማዕቀፎች እንዲጠናከሩ እየተደረገ መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ምስጋኑ፣ በሁለትዮሽ ግንኙነት የተጀመረው ግንኙነታቸው ቀጠናዊ በሆኑ የጋራ ጉዳዮችም እንደሚጠናከር አስታውሰዋል።

የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስትር ቢልዋል ቡቶ ዛዲሪ በበኩላቸው፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማድረስ በሁለቱ ሀገራት መንግሥታት አበረታች ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካራቺ አዲስ የቀጥታ በረራ መጀመሩ ለግንኙኘታቸው እየተጠናከረ መምጣት ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከአንድ ዓመት በፊት በኢዝላማባድ ኤምባሲዋን መክፈቷ በግንኙነታቸው አዲስ ምዕራፍ መክፈቱንም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛዲሪ አስታውሰዋል።

ወደ ፓኪስታን በማምራት የዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች እያከ