4ኛው ዙር የኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ

10 Mons Ago 394
4ኛው ዙር የኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ

የአሁኑ ድርድር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ በሐምሌ ወር መጀመሪያ ተገናኝተው የሰጡትን የጋራ መግለጫ ተከትሎ እየተካሄደ ያለ ነው። 

መሪዎቹ በውይይታቸው የሶስቱ ሀገራት ተወካዮች ድርድሩን በማፋጠን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት እና ቀጣይ ተግባራትን የተመለከቱ መመሪያዎች እና ደንቦችን እንዲያዘጋጁ ከመግባባት ደርሰው እንደነበር ከዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። 

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን መሪ አምባሳደር ስለሺ በቀለ እንዳሉት፥ በሚኒስትሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ድርድር ዓላማ ቀደም ሲል የተካሄዱ ውይይቶችን በማዳበር ከጋራ መግባባት ላይ መድረስ ነው። 

በዚህ ድርድር ኢትዮጵያ እኤአ በ2015 የተደረሰበትን የመርሆች ስምምነት መሰረት በማድረግ እንደምትሳተፍ አምባሳደር ስለሺ ጠቁመዋል። 

ሀገሪቱ ከድርደሩ በጋራ መግባባት እንዲሁም በፍትሃዊ እና ምክንያታዊ የዓባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ የተመሰረተ ውጤት እንዲመጣ ጥረት ማድረጓን ትቀጥላለችም ብለዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top