በጅቡቲ ፓርላማ አፈ ጉባኤ የተመራው የሀገሪቱ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ

10 Mons Ago 470
በጅቡቲ ፓርላማ አፈ ጉባኤ የተመራው የሀገሪቱ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የጅቡቲ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ዲሌታ መሀመድ ዲሌታ እና የልዑካን ቡድናቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። 

ከውይይቱ በተጨማሪ በቆይታቸው የአየር መንገዱን የተለያዩ የስራ ክፍሎች ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top