ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በካርበን ሽያጭ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል በሚቻልባቸው ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ

12 Hrs Ago 48
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በካርበን ሽያጭ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል በሚቻልባቸው ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በካርበን ሽያጭ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል በሚቻልባቸው ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።
 
ከዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደው የሁለቱ ሀገራት ውይይትና ስምምነት፣ ኢትዮጵያ የደን ሽፋኗን ለመመለስ እና የአየር ንብረት ለውጥን በዘላቂነት ለመቋቋም የምትሰራውን ስራ ለመደገፍ እንዲሁም በካርበን ሽያጭ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ነው የተፈረመው።
 
በካርበን ሽያጭ እንዲሁም በደን ክብካቤ እና አጠባበቅ ዙሪያ ቴክኒካዊ ድጋፎችን ለማድረግ ስምምነቱ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
 
የብሪክስ አባል የሆኑት ሁለቱ ሀገራት ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን ሙቀት አማቂ ጋዝ ለመቀነስ፣ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን አረንጓዴ አሻራ ለመደገፍ እና በካርበን ሽያጭ ላይ በጋራ ለመስራት በመስማማት ፊርማ ማኖራቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ( ዶ/ር ) ተናግረዋል።
 
በተመስገን ሽፈራው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top