የሀረሪ ክልል ምክር ቤት የቀረበለትን የካቢኔ አባላት ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።
የካቢኔ አባላት ሹመት በምክር ቤቱ የጸደቀው በክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አቅራቢነት ነው።
በዚህ መሰረትም ፡-
1ኛ ወ/ሮ ሮዛ ኡመር - የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ
2ኛ ወ/ሮ ኢክራም አብዱልቃድር - የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
3ኛ አቶ አሰፋ ቶልቻ- የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ
4ኛ አቶ ኡስማኤል ዩሱፍ- የክልሉ ኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ
5ኛ ወ/ሮ ረምዚያ አብዱልወሃብ- የክልሉ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
6ኛ አቶ ቶፊቅ መሀመድ- የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
7ኛ አቶ መሀመድ ያህያ- የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ
8ኛ አቶ ያሲን አብዱላሂ- የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ
9ኛ ወ/ሮ ደሊላ ዩሱፍ- የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
10ኛ አቶ አብዱማሊክ በከር- የክልሉ ዋና ኦዲተር
በተጨማሪም በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ አቅራቢነት በተጓደሉት የክልሉ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ እና አባላትን ሰይሟል
በዚሁ መሰረት
1ኛ አቶ ጌቱ ወዬሳ- የክልሉ የብዙሃን መገናኝ ኣጀንሲ ቦርድ ሰብሳቢ
2ኛ አቶ መሀመድ ያህያ- የክልሉ የብዙሃን መገናኝ ኣጀንሲ ቦርድ አባል
3ኛ አቶ ቶፊቅ መሀመድ-የክልሉ የብዙሃን መገናኝ ኣጀንሲ ቦርድ አባል እንዲሆኑ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
በክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አሪፍ መሀመድ አቅራቢነት
1ኛ አቶ ጅብሪል መሀመድ- የክልሉ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ
2ኛ ወ/ሮ ፊቲያ ሳኒ - በክልሉ ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሰቢ ሆነው እንዲያገለግሉ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን የክልሉ ከሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመልክቷል።