የአፍሪካ ህብረት አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣቷን ውሳኔ እንድታጤነው ጠየቀ

20 Hrs Ago 125
የአፍሪካ ህብረት አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣቷን ውሳኔ እንድታጤነው ጠየቀ

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት አሜሪካ ከዓለም ጤና ድርጅት አባልነት የመውጣቷን ውሳኔ መልሳ እንድታጤነው ጠይቀዋል፡፡

ሙሳ ፋኪ አሜሪካ ከድርጅቱ አባልነት ለመውጣት መፈለጓ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፤ ውሳኔውን መለስ ብሎ በማጤን በአባልነቷ ትቀጥላለች የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የአፍሪካ ህብረት ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካ የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከል (አፍሪካ ሲዲሲ) መስረታ ላይ ቀደምት እና ጠንካራ ደጋፊ ነበረች ብሏል፡፡

አሁን ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዓለም አቀፉን የህብረተሰብ ጤና ደህንነት እንደ አንድ የጋራ ጥቅም የማረጋገጥ ተልዕኮውን ለመወጣት በዓለም ጤና ድርጅት ላይ ጥገኛ መሆኑን የገለፀው ህብረቱ፤ የድርጅቱ ቁልፍ መስራች አባል የሆነችው አሜሪካ ከተቋሙ ለመውጣት ያቀደችውን ውሳኔ በድጋሚ እንድታጤነው ጠይቋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top