2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር ተጠናቀቀ

21 Hrs Ago 180
2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን የማጠቃሊያ ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።

በማጠቃሊያ ውድድሩ በቁርዓን ሂፍዝ፣ በቁርዓን ቲላዋ እና በአዛን ዘርፍ አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች በዳኞች አማካኝነት ይፋ ሆነዋል።

በዚህም

በወንዶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር

1ኛ. ሙሐመድ ፉዓድ … ከሊቢያ

2ኛ. ዩሱፍ አሺር … ከኳታር

3ኛ. አህመድ በሺር …ከአሜሪካ

በሴቶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር

1ኛ ሩቅያ ሳላህ … ከየመን

2ኛ ነሲም ጀናዉጃ … አልጄሪያ

3ኛ ቀመራ ወሊዩ መሐመድ … ከኢትዮጵያ

በአዛን ውድድር

1ኛ ሙሀመድሻን አቡበከር … ከኢንዶኖዢያ

2ኛ ኡመር ዱራን … ከቱርክ

3ኛ አደም ጅብሪል … ከኢትዮጵያ

በወንዶች የቁርአን ቲላዋ ውድድር

1ኛ አብዱራዛቅ አል ሸሀዊ …ከግብፅ

2ኛ ከራር ለይስ … ከኢራቅ

3ኛ አንጀድ ካምዳን … ከየመን አሸናፊ ሆነዋል፡፡

ጥር 21 ተጀምሮ ዛሬ በተጠናቀቀው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን ውድድር ላይ ከ60 በላይ ሀገራት ተሳትፈዋል ተብሏል።

በማጠቃሊያ ውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማዕ ጽህፈት ቤት፣ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ስራ አስፈፃሚዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች መታደማቸውን የጠቅላይ ምክር ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top