በጋምቤላ ክልል የተፋሰስ ልማት ስራ ተጀመረ

3 Hrs Ago 47
በጋምቤላ ክልል የተፋሰስ ልማት ስራ ተጀመረ

በጋምቤላ ክልል የዘንድሮው የተፋሰስ ልማት ስራ በክልል ደረጃ በማጃንግ ዞን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በዚሁ ወቅት፤ በጋምቤላ ክልል በተፋሰስ ልማት የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ማህበረሰቡ የነቃ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በክልሉ ባለፉት ዓመታት የተፋሰስ ልማትን ከግብርና ልማት ስራዎች ጋር በማቀናጀት     ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን  ገልፀዋል።

በዚህም ማህበረሰቡን በማሳተፍ የአፈር ለምነትን የሚያሻሽሉ ስራዎች መከናወናቸውን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሯ፤ በተፋሰስ ልማት እስካሁን የተገኙ ውጤቶችን ለማስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ማህበረሰቡም በተፋሰስ ልማት ስራ ተሳትፎውን ሊያጠናክር እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሯ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የክልሉ እርሻና የተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፓል ቱት በበኩላቸው፤ በዘንድሮው የበጋ ወራት ከ145 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የሚሸፍን የተፋሰስ ልማት ሥራ እንደሚከናወን ገልፀዋል፡፡

የማጃን ዞን ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ ባለፉት ተከታታይ አመታት ያከናወኑት የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ በአካባቢያቸው የአፈር ለምነት እንዲሻሻልና የተስተካከለ ስነ-ምህዳር እንዲፈጠር ማስቻሉን ገልፀዋል፡፡

በሚፍታህ አብዱልቃድር


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top