“በተለያዩ አካባቢዎች በሰማይ ላይ የታየውን ተቀጣጣይ የሚመስል ቁስ ምንነት እያጣራሁ ነው”፦ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ

4 Hrs Ago 53
“በተለያዩ አካባቢዎች በሰማይ ላይ የታየውን ተቀጣጣይ የሚመስል ቁስ ምንነት እያጣራሁ ነው”፦ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ
በትናንትናው ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች ምንነቱ በውል ያልታወቀ በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ የሚታይ ተቀጣጣይ ነገር መመልከታቸውን በርካቶች የአካባቢው ነዋሪዎች በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ በተንቀሳቃሽ ምስል እና በፎቶ አስደግፈው ሲያጋሩ ተስተውሏል።
 
ይህንንም ተከትሎ ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ ምንነት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አስታውቋል።
 
የክስተቱን ምንነት በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችል ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራሁ ነው ያለው ተቋሙ የተጣራ መረጃ ሲደርስም ለህብረተሰቡ ይፋ እንደሚደረግ እና የማጣራት ሥራው እስኪጠናቀቅ ሁሉም ሰው በተረጋጋ መንፈስ እንዲጠባበቅ አስታውቋል።
 
ተቋሙ በታዩት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ለመመልከት እንደቻለውም የእነዚህ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አሊያም የሚቲዮር አለቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ መላምቱን አስቀምጧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top