በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአማራ ክልል ሁለተኛው ምዕራፍና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ የማስጀመሪያ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከመንግስት አካላት፣ ከማኀበራት፣ ከተፅዕኖ ፈጣሪዎችና ተቋማት የተወከሉ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች፣ ተሳታፊ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ከመጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው የክልሉ የምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ፣ የመጀመሪያውና 10 የማህበረሰብ ክፍሎችን የወከሉ ከ4 ሺህ 500 በላይ ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን አሰባስበው በትናንትናው ዕለት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።
ዛሬ የጀመረው የባለድርሻ አካላት ምክክር እስከ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ይቀጥላል።