በአሜሪካ 8 ግዛቶችን በመታው አውሎንፋስ የ42 ሰዎች ሕይወት አለፈ

1 Day Ago 111
በአሜሪካ 8 ግዛቶችን በመታው አውሎንፋስ የ42 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በምስራቅ እና ምዕራባዊ የአሜሪካ ክፍል በተከሰተ ከፍተኛ አውሎ ንፋስ የ42 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ከባድ ውድመትንም አስከትሏል፡፡
 
አቧራ የቀላቀለው እና ሰደድ እሳትን ያስከተለው አውሎ ንፋሱ በ8 ግዛቶች ላይ ውድመትን አድርሷል፡፡
 
ሚዙሪ፣ ካንሳስ እና አላባማ ከፍተኛ የሟች እና የውድመት መጠንን በቅደም ተከተል ያስተናገዱ ግዛቶች ናቸው፡፡
 
አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረው አደጋው ለመብራት እና የትራንስፖርት መቋረጥ፣ ለትምህርት ቤቶች እና አውራ ጎዳናዎች መዘጋት እንዲሁም ለርካታ አገልግሎቶች መስተጓጎል ምክንያት ሆኗል፡፡
 
ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአደጋው ተጋላጭ መሆናቸው በአየር ትንበያ መረጃ ተመላክቷል፡፡
 
ይህንንም ለመቋቋም የግዛቱ አመራሮች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጁ ሲሆን ከፌደራል መንግስት እገዛን እየጠየቁም ይገኛሉ፡፡
 
በአደጋው ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ዜጎች አስፈላጊ ሁኔታዎችን ለማሟላት እየተሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ዜጎች ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ መሰጠቱን ሲኤንኤን በዘገባው ጠቁሟል፡፡
 
በአፎሚያ ክበበው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top