የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ለተነሡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ ዋና ዋና ነጥቦች

7 Hrs Ago 1378
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በወቅታዊ የክልሉ ሁኔታ ላይ ለተነሡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ ዋና ዋና ነጥቦች

 • የፕሪቶሪያው ስምምነት ያጨናገፈባቸውን መንገድ አሁን በትግራይ የተፈጠረውን አጋጣሚ በመጠቀም የትግራይን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ የተዘጋጁ ወገኖች አሉ

• የፌዴራል መንግሥት እንደዚህ ዓይነት ግጭት እንዳይከሰት በቂ ጥረት አድርጓል። ይህ ችግር እንዲከሰት ያደረጉት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያሉ ጥቂት አካላት ናቸው።

• ማሕተም የሚነጥቀው ቡድን ምንም ዓይነት የሐሳብ ልዩነትን ለመቀበል ፍላጎት የሌለው ነው። ሥልጣን ያስገኝልኛል ያለውን የትኛውን ትርምስ ለመፍጠር የተዘጋጀ ኃይል አለ።

• ፌዴራል መንግሥት የሠራቸውን በጎ ነገሮች መጥቀስ በዚህ ቡድን ተወቃሽ እያደረገኝ ስለሆነ የፌዴራል መንግሥት ለመውቀስ እየተገደድኩ ነበር።

• የትግራይ ሕዝብ መሔድ ወደሚፈልገው ሳይሆን መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው ያለው።

• የትግራይ ሕልውና ያስፈልጋል ብሎ የሚያምን አካል ሁሉ የሚቻለውን ማድረግ አለበት።

• የፕሪቶሪያ ስምምነት ዓላማ ተኩስ ማቆም ነው፤ የተስማማነውም አንድ መከላከያ ሠራዊት ብቻ እንዲኖር ነው።

• በክልሉ በርካታ መሠረተ-ልማቶች እንዲጠፉ ተደርገዋል።

• የኢኮኖሚ ዳግም ግንባታ ለማድረግ የሰላም ሁኔታዎችን መፍጠር አስፈላጊ ነው ብሎ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ያምናል።

• ለምሳሌ የ‘ዲዲአር’ (ተሃድሶ) ለመፈፀም የሚደረገው ጥረት በቂ አይደለም። አሁን ባለው ሁኔታ ምክንያት ሂደቱ በትክክል እየሄደ አይደለም።

• የተሃድሶ ሂደቱን ከማስቆም አንፃር ተጠያቂው እኛ ነን፤ የፌዴራል መንግሥቱ አይደለም። ለዚህ የፌዴራል መንግሥትን መውቀስ አልችልም።

• በተገኘው አጋጣሚ ወደ ድሮ ሥልጣኔ ልመለስ የሚለው ኃይል ትርምሱ በመቐለ ጭምር እንዲካሄድ እያደረገ ነው።

• የፌዴራሉን መንግሥት ተችቼ እንድጽፍ ተገድጄ ነበር ግን እኛው ራሳችን በፈጠርነው ትርምስ ነው ዲዲአሩ የተቋረጠው።

• የፌዴራል መንግሥትን ከሚፈለገው በላይ ተችቻለሁ፤ አምባሳደር በመጣ ቁጥር የፌዴራል መንግሥትን ወቅሻለሁ።

• ተፈናቃዮች እንዳይመለሱ ያደረግነው ራሳችን ነን፤ ምክንያቱም እነሱ ሲመለሱ አጀንዳ ይጠፋል በሚል።

• ለዚህ የፌዴራል መንግሥቱን ለምንድን ነው ሁሌም የምንወቅሰው? መወቀስ የለበትም።

• እኔ ባለሁበት ፓርቲ ውስጥ ባለው የተምታታ እሳቤ ከፌዴራል መንግሥት ጋር መሥራት በባንዳነት የሚያስፈርጅ ነው።

• ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሔጄ የነጋዴን እና የገበሬን ጉዳይ ማስረዳት ሲገባኝ በባንዳነት እንዳልፈረጅ እየሰጋሁ ነው።

• ሥልጣንን ብቻ ዒላማ ያደረገው ቡድን ነው ይህን ነገር የሚፈጥረው፤ ሠራዊቱ ትርምስ አይፈጠረም።

• ካሜራ ፊት ባይሆንም በጎን በድብቅ ወደ ወንበሬ መልሰኝ በሚል ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚጠይቁ አሉ።

• ሰላም ሲፈጠር እያዛለሁ፣ ፌዴራል መንግሥት ይይዘናል በሚል የሚፈሩ አሉ፤ እነዚህ ጥቂት ሰዎች ናቸው ሰላም እንዳይፈጠር የሚያደርጉት።

• ወጣቱ ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለስ ይፈልጋል። ይህንን ኃላፊነት ወደ ፌዴራል መንግሥቱ ብቻ መስጠት አያስፈልግም።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top