ለተፈናቃይ ዜጎች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተጠቆመ

1 ዓመት በፊት 335
ለተፈናቃይ ዜጎች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተጠቆመ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ ለተፈናቃይ ዜጎች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አሳስቧል።

ቋሚ ኮሚቴው በሶማሌ ክልል፣ ባቢሌ ወረዳ በመጠለያ ጣቢያ ያሉ ተፈናቃይ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ (ዶ/ር) ዜጎች ለረጅም ጊዜ በመጠለያ ውስጥ መቆየታቸው አግባብ አለመሆኑን ጠቁመው፤ ለቀጣይ የፌደራል እና የክልል መንግሥታት በቅንጅት ለችግሩ ዘላቂ የሆነ መፍትሄ መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ሰብሳቢው አያይዘውም፥ ዜጎች በውጭ ድርጅቶች ተረጂ ሆነው መኖር ስለሌለባቸው ለመልሶ ማቋቋም ስራው የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት፥ እንደ የሕዝብ ተወካይ ተፈናቃይ ዜጎቹ ያሉባቸው ችግሮች እልባት እንዲያገኙ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።

የባቢሌ መጠለያ ጣቢያ አደጋ ስጋት እና መልሶ ማቋቋም ኃላፊ አቶ ሄኖክ በየነ በበኩላቸው፥ የሰው ልጅ ዕድሜ ልኩን ተረጂ መሆን ስለሌለበት ተፈናቃይ ዜጎችን ወደነበሩበት መመለስ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ማለታቸውን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top