የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መከበር ኅብረ ብሔራዊት ሀገር ለመገንባት ሚናው የጎላ ነው - አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ

10 Mons Ago 361
የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መከበር ኅብረ ብሔራዊት ሀገር ለመገንባት ሚናው የጎላ ነው - አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን መከበር የምናስባትን አካታችና ኅብረ ብሔራዊት ሀገር ለመገንባት ሚናው የጎላ ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ።

አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ የ18ኛው ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባባርን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በጅግጅጋ መከበር ልዩ ትርጉም እንዳለው አንስተዋል።

በዓሉ በታቀደው መልኩ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑን ገልፀው፤ የፀጥታ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም አስተማማኝ ዝግጅት አድርገው ወደ ስራ መግባታቸውን ጠቁመዋል።

በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውን እንዲለዋወጡ እና ማንነታቸውን እንዲያሳዩ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች  ቀን በዓል መከበር አካታችና ኅብረ ብሔራዊት ሀገር ለመገንባት ሚናው የጎላ ነው ሲሉም አውስተዋል።

በዓሉ በክልሉ መከበሩም ለቀጣይ በርካታ ልምዶችና ተሞክሮዎችን እንደሚያስገኝ መናገራቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top