የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጅግጅጋ በእሳት አደጋ ለተጎዱ አካላት የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

10 Mons Ago 1157
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጅግጅጋ በእሳት አደጋ ለተጎዱ አካላት የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጅግጅጋ ከተማ በእሳት አደጋ የንግድ ተቋማቸው ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውል የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ አስረክበዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በዚሁ ወቅት፥ የድጋፉ ዋና ዓላማ በእሳት አደጋው ጉዳት ያስተናገዱ ወገኖቻችን ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት አብሮነትን ለማሳየት ነው ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ በበኩላቸው፥ በእሳት አደጋ ምክንያት በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ሂደትም ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመው፥ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የማጠቃለያ የዋዜማ ዝግጅት በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ በደማቅ ሥነ-ስርዓት ተካሂዷል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top