የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ይዘቶች አብሮነትን ያስቀደሙ እና የሌላውን እምነት ያከበሩ ሊሆን እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ መገናኛ ብዙሃኑ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ መቻቻልና አብሮነትን ለማጠናከር አበክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በኢትዮጵያ በርካታ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን እንደሚገኙ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ ተቋማቱ ትውልድ ለማነጽ እና ሀገር ለመገንባት ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል፡፡
የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ በበኩላቸው ፤ አዲሱ የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ የሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ህጋዊ ሰውነት እንዲኖራቸው ማስቻሉን ተናግረዋል።
መድረኩ ለሀገር ሰላምና አንድነት መጎልበት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መሆኑንም አንስተዋል።
የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ከሃይማኖት መገናኛ ብዙሃን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በሰላም ግንባታ ዙሪያ የምክክር መድረክ እያካሄደ መሆኑን ኢ