የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በተመራማሪዎቹ ያሰራቸውን ማሽኖች ለክልሎች አበረከተ

22 Hrs Ago 114
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በተመራማሪዎቹ ያሰራቸውን ማሽኖች ለክልሎች አበረከተ
የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በተመራማሪዎቹ ያሰራቸውን የእንጨትና የብረት ቅርጽ ማውጫ ማሽኖች ለአምስት ክልሎች አበርክቷል።
 
ማሽኖቹ በተቋሙ ባለሙያዎች የለሙና በራስ አቅም የተሰሩ መሆናቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል።
 
በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ አምስት የፕላዝማ እና ራውተር ሲ. ኤን. ሲ ማሽኖችን ለአማራ፣ ትግራይ፣ ሲዳማ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ነው ያስረከበው።
 
ማሽኖቹ በብረትና እንጨት ላይ ቅርጾችን ለማውጣት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ገልጸው፤ በክልሎች ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የሚውሉ መሆኑንም ተናግረዋል።
 
የክልሎቹ ተወካዮች በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ ማሽኖቹን ከማስረከብ ባለፈ በአጠቃቀሙ ላይ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረጉን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top