በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራው የሚፈርሱ ቤቶች በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት ያላሟሉ ናቸው - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን

6 Mons Ago 462
በመዲናዋ በኮሪደር ልማት ስራው የሚፈርሱ ቤቶች በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት ያላሟሉ ናቸው - የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሪደር ልማት ስራ ምክንያት የሚፈርሱ ቤቶች በቅርስነት ለመመዝገብ የሚያስችል መስፈርት የሚያሟሉ ባለመሆናቸው ነው ሲል የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ገለፀ፡፡

ባለስልጣኑ ከአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጉዳዮችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል::

መግለጫውን የሰጡት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፤ በኮሪደር ልማቱ የሚፈርሱ ቤቶች በአብዛኛው የቅርስነት መስፈርትን የማያሟሉ ናቸው ብለዋል::

ቤቶቹን በቅርስነት ለመመዝገብ ያላቸው ታሪክ፣ አሁን ያሉበት ውጫዊ እና ውስጣዊ ገፅታ፣ እድሜያቸው፣ አርክቴክቸርን ጨምሮ በርካታ መስፈርቶች መቀመጣቸውን ገልጸዋል::

በተቀመጡት መመዘኛዎች መሰረት ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጣ በቅርስነት እንደሚመዘገብ እና በአንጻሩ ከ50 በታች የሆነ ቤት ቅርስ ተብሎ ሊመዘገብ እንደማይችል ጠቁመዋል::

ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የቅርስ መስፈርቶችን ያላሟሉ ሁሉ የተመዘገቡ መኖራቸውን አስታውሰው፤ በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት በአዲስ መልክ የቅርስ ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚሁ መሰረት ከዚህ በፊት የተመዘገቡ በቅርስነት የሚቀጥሉ ሲኖሩ በመመሪያው መሰረት መስፈርቱን የማያሟሉ ደግሞ የማይቀጥሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የልማት ስራና ቅርስ የማስጠበቅ ሂደት ተጣጥሞ መሄድ እንዳለበት የጠቀሙት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የሀገር ከፍተኛ ትርጉም ያላቸውን ቅርሶችን መጠበቅ እና መንከባከብ ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቅሰዋል::

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን የባለሙያዎች ቡድን በኮሪደር ልማቱ የሚፈርሱ ቤቶች ላይ የክትትልና የቁጥጥር ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል::

በአለም ይልፉ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top