የከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ለሃገር ከፍ ያለ አበርክቶ እንዳይኖረው አንቀው ከያዙት ማነቆዎች ሊላቀቅ እንደሚገባ ተገለጸ

7 Mons Ago 296
የከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ለሃገር ከፍ ያለ አበርክቶ እንዳይኖረው አንቀው ከያዙት ማነቆዎች ሊላቀቅ እንደሚገባ ተገለጸ

የከፍተኛ ትምህርት ፕሬዝዳንቶች ፎረም "ከፍተኛ ትምህርት ከፍ ላለ ተጽዕኖ" በሚል መሪ ቃል በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ በዘርፉ የሚተገበሩ አዳዲስ ሪፎርሞች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል::

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሸኔ በውይይት መድረኩ ተገኝተው ካለፈው ተሞክሮ ስለተገኙ ቁም ነገሮችና ዘርፉ ያለበትን ቁመና አስመልክቶ ንግግር አድርገዋል::

ሚኒስትር ዴኤታው ባስተላለፉት መልዕክት የከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ለሃገር ከፍ ያለ አበርክቶ እንዳይኖረው አንቀው ከያዙት ማነቆዎች ሊላቀቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለፎረሙ ተሳታፊዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቂ ነጻነት ፍኖተ-ካርታ፣ የዩኒቨርስቲዎች ትኩረት መስክ እና ተልዕኮ ልየታ፣ በከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና፣ የምርምር ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ትስስር አዋጅ 1298/2015 ጨምሮ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፉ ላይ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ ስላሉ አዳዲስ ትግበራዎች እና የለውጥ አጀንዳዎች ዙሪያ የውይይት ነጥቦች ቀርበዋል::

በፎረሙ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የትምህርት ሚኒስቴር እና የጅማ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የፎረሙ መድረክ ትናንት የተጀመረ ሲሆን በቀረቡ ሰነዶች ላይ በመወያየት እና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን በማመላከት ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top