በመውጫ ፈተና የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ተሰረዘ

7 Mons Ago 547
በመውጫ ፈተና የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ተሰረዘ

በመውጫ ፈተና ሞባይል ስልክ ይዞ በመግባት፣ በመኮረጅና የተለያዩ የፈተና ስነ-ምግባር ጥሰት የፈጸሙ 114 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ መሠረዙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የፈተና ስነምግባር ጥሰት የፈጸሙት 114 ተፈታኞች ውጤታቸው ሙሉ በሙሉ መሠረዙን እና የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች በቀጣይ የሚገለጽ መሆኑን ሚኒስቴሩ ጠቅሷል።

ከየካቲት 6 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ የመንግስት ተቋማት በተሰጠው ሁለተኛ ዙር የመውጫ ፈተና 119 ሺህ 145 ተፈታኞች ፈተናውን መውሰዳቸው ተጠቁሟል።

ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ጥራትን ለማረጋገጥ ከጀመራቸው ሪፎርሞች አንዱ የሆነው መውጫ ፈተና ተመራቂዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ተገቢውን እውቀትና ክህሎት መቅሰማቸውንና ብቁ መሆናቸውን ዒላማ ያደረገ በመሆኑ ፈተናው በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top