የፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ጉዞ ወሳኝ ጨዋታ አርሴናል ከሊቨርፑል ምሽት 1 ከ30 ይካሄዳል

8 Mons Ago 503
የፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ጉዞ ወሳኝ ጨዋታ አርሴናል ከሊቨርፑል ምሽት 1 ከ30 ይካሄዳል

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የሊጉ የዋንጫ ጉዞ ወሳኝ ጨዋታ አርሴናል ከሊቨርፑል ዛሬ ምሽት 1 ከ30 ይካሄዳል።

ሊቨርፑል በፕሪሚየር ሊጉ በ22 ጨዋታዎች 51 ነጥብ በመሰብሰብ በሊጉ አናት ላይ ተቀምቷል።

አርሴናል በበኩሉ በተመሳሳይ በ22 ጨዋታዎች 46 ነጥብ በመሰብሰብ በማንቸስተር ሲቲ በግብ ክፍያ ተበልጦ (ሲቲ አንድ ጨዋታ እየቀረው) ከሊጉ መሪ በ5 ነጥብ ዝቅ ብሎ በ3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የአርሴናሉ አሰልጣኝ ማይክል አርቴታ ከጨዋታው በፊት በሰጠው አስተያየት፥ "ተጋጣሚያችን ጠንካራ ቡድን በመሆኑ ለዚህ የሚሆን ዝግጅት አድርገናል። ቶማስ ፓርቴ በጉዳት አሁንም አይሰለፍም፤ ጋብሪኤል ሄሱስ ግን ወደ ሜዳ ይመለሳል። በውድድር ዓመቱ ትላልቅ ቡድኖችን ማሸነፍ ችለናል። ዛሬም ያንን  ድል ለማድገም ትልቅ ዕድል አለን። የምንጫወተው በሜዳችን በመሆኑ ልዩ ድባብ እንደሚኖረው እጠብቃለሁ። ደጋፊዎቻችንም ከጎናችን እንዲሆኑ ማሳሰብ እወዳለሁ" ብሏል።

የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በበኩላቸው፥ "ተጋጣሚያችን ጠንካራ ቡድን በመሆናቸው እነሱን ማሸነፍ ከባድ ነው። አርሴናልን  በ5 ነጥብ ልዩነት እመራን ነው፤ ካሸነፍን ልዩነቱን ወደ 8 ማስፋት እንችላለን፤ ከተሸነፍን ደግሞ አሁንም በ2 ነጥብ ልዩነት መምራታችንን እንቀጥላለን፤ ብዙ ማሻሻል ያሉብን ክፍተቶች ማረም ላይ በትኩረት እየሰራን ነው፤ ሁሉም ሊዘነጋው የማገባው ነገር ግን ማንቸስተር ሲቲ ለዋንጫው ጠንካራ ተፎካካሪ ከሆኑ ክለቦች መካካል አንዱ ነው። በልምምድ የሰራነውን ወደ ውጤት መቀየር በሜዳ የሚታይ ይሆናል" ብለዋል።

ሁለቱ ክለቦች ከዚህ ቀደም በፕሪሚየር ሊጉ ካደረጓቸው 17 ጨዋታዎች አርሴናል ማሸነፍ የቻለው ሁለት ጊዜ ብቻ ሲሆን፤ እነሱም እኤአ በ2020 እና በ2022 ነው።

ዛሬ ከ11 ሰዓት ጀምሮ ቼልሲ ከዎልቨርሃምፕተን፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር እንደሚጫወቱ ይጠበቃል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top