በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች መንግሥት አፋጣኝ ሰብአዊ እርዳታ እያደረሰ ነው፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

9 Mons Ago 207
በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች መንግሥት አፋጣኝ ሰብአዊ እርዳታ እያደረሰ ነው፡- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

መንግሥት ከተለየዩ አካላት ጋር በመተባበር አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈለጋቸው 3.8 ሚሊዮን ወገኖች እርዳታ ማድረሱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ፤ ለሰብዓዊ እርዳታው በሦስት ተከታታይ ዙሮች 15 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 40 በመቶውን የፌዴራል መንግሥት፣ 60 በመቶውን ደግሞ የዓለም ባንክ እንደሸፈነው ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም በድርቅ እና በተለያዩ ምክንያቶች ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ9 ሚሊዮን በላይ ወገኖች ተለይተው እርዳታውን ከጥር እስከ የካቲት ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለነዚህ ወገኖች የሚደርሰውን እርዳታ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ ለዚህም 9.2 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በፌዴራል መንግሥት በኩል አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ያልተቋረጠ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ አየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ፣ የክልል መንግሥታትም የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ለእነዚህን ወገኖች ለመድረስ የእርዳታ ድርጅቶችን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top