በ2023 የአፍሪካ ዋንጫ፥ የአፍሪካ ሻምፒዮናነት የክብር ዘውዱን ማን ይደፋው ይሆን?

9 Mons Ago 589
በ2023 የአፍሪካ ዋንጫ፥ የአፍሪካ ሻምፒዮናነት የክብር ዘውዱን ማን ይደፋው ይሆን?

በ2023 የአፍሪካ ዋንጫ፥ የአፍሪካ ሻምፒዮናነት የክብር ዘውዱን ማን ይደፋው ይሆን?

************************

የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የፊታችን ቅዳሜ አዘጋጅዋ ኮትዲቯር ከጊኒ ቢሳው በሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ይጀምራል። የ2023 ይባል እንጂ፣ ውድድሩ እየተካሄደ ያለው በ2024 መባቻ ላይ ነው። የሆነ ሆኖ፥ ዋንጫውን ማን ያነሳው ይሆን? የ2021 ሻምፒዮኗ የሳዲዮ ማኔዋ ሴኔጋል ደግማ ትወስደው ይሆን? ሴኔጋል ዋንጫውን ደግማ የመውሰድ እድሏ ምን ያህል ነው? በ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የአፍሪካ ሻምፒዮናነት የክብር ዘውዱን ማን ሊደፋ ይችላል? የ2021 ሻምፒዮኗ ሴኔጋል፣ የዓለም ዋንጫ ክስተቷ ሞሮኮ ወይስ ግብ አዳኟ ናይጄሪያ? ቢቢሲ ኦፕታ ከተሰኘው የብሪታኒያ የስፖርታዊ ትንተና ኩባንያ ጋር በመሆን ትንበያውን በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ቀምሮታል። 

በኦፕታ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ትንበያ ሞዴል መሠረት፥ በጠባብ ልዩነትም ቢሆን ሴኔጋል ዋንጫውን የማንሳት ቅድሚያ ግምት አግኝታለች። በዚህም ተከታታይ የአፍሪካ ዋንጫዎችን በማሸነፍ አራተኛዋ አገር ትሆናለች። በዚህም ዋንጫውን በተከታታይ በማሸነፍ ከግብፅ ወዲህ የመጀመሪያዋ አገር ትሆናለች። ግብፅ በ2006 እና በ2010 መካከል የአፍሪካ ዋንጫን ለ3 ተከታታይ ጊዜያት ማሸነፏ ይታወሳል። በነገራችን ላይ ባለፉት 6 የአፍሪካ ዋንጫዎች አሸንፈው ዋንጫ ካነሱ አገራት መካከል በተከታይ የአፍሪካ ዋንጫ የ16ቱን ምድብ ተሻግሮ ሩብ ፍፃሜ የደረሰ አንድም ቡድን የለም። 

እናም በዚሁ የኦፕታ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ትንበያ ሞዴል መሠረት፥ ሴኔጋል 12.8 በመቶ የማሸነፍ ዕድል ይዛ በ1ኛ ደረጃ ላይ የተሰየመች ሲሆን፤ አዘጋጇ ኮትዲቯር 12.1 በመቶ የማሸነፍ ዕድል ኖሯት በ2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ኮትዲቯር የዘንድሮው ከተሳካላት የ1992 እና የ2015ን ጨምሮ ዋንጫውን ለ3ኛ ጊዜ የምታሸንፍ ይሆናል። ሻምፒዮናውን አዘጋጅታ ዋንጫውን በማስቀረትም ግብፅን ተከትላ ሁለተኛዋ አገር ትሆናለች። 

በትንበያው መሠረት፥ ሞሮኮ 11.1 በመቶ የማሸነፍ ዕድል ተሰጥቷት በ3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። አልጄሪያ፣ ግብፅ፣ ናይጄሪያ፣ ካሜሩን፣ ቱኒዚያ እና ጋና በቅደም ተከተል ቀጣይ ግምት ካገኙ አገራት መካከል ናቸው። እርስዎስ፥ በትንበያው ይስማማሉ? የማይስማሙ ከሆነ፥ የአሸናፊነት ቅድሚያ ግምት የሚሰጡት ለማን ነው?


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top