በቀጣይ ሦስት ወራት ለ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ይደረጋል

9 Mons Ago 215
በቀጣይ ሦስት ወራት ለ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ይደረጋል

መንግሥት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በቀጣይ ሦስት ወራት ለ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እንደሚያደርግ የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ገለጹ።

ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም፤ በሀገሪቱ አሁን ላይ ወደ 4 ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከል 80 በመቶው የሚሆኑት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች የሚገኙ መሆኑን ጠቅሰው በድርቅ ምክንያት በርካቶች ለችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል።

በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች 1 ነጥብ 5 ሚለየን ዜጎች በጎርፍና በተያያዥ ችግሮች ለተለያዩ ሰብዓዊ ችግሮች መጋለጣቸውን ጠቅሰዋል።

መንግሥት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር በቀጣይ ሦስት ወራት ማለትም ጥር፣ የካቲትና መጋቢት ለ6 ነጥብ 6 ሚሊየን ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ ለማድረግ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። 

በድርቅ ምክንያት በሚከሠት ችግር የሠው ህይወት እንዳይጠፋና የሚያስፈልገውን የሠብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ለመሸፈን መንግስት በልዩ ትኩረት እየሠራ መሆኑንም ጨምረው ጠቅሰዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ሰብዓዊ ድጋፍ በባህሪው ዓለም አቀፍ ድጋፍ የሚያስፈልገው መሆኑን ተናግረው ዓለም አቀፍ የረድኤት ተቋማት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

 

ቀደም ሲል መንግሥት ከአጋር አካላት ጋር በመሆን 15 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚገኙ ከ7 ሚሊየን በላይ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ መደረጉ ይታወሳል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top