ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

9 Mons Ago 299
ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ሀሰተኛ ሰነድ በሚያዘጋጁ ግለሰቦች ላይ ባደረገው ክትትል ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሠነዶችንና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚገለገሉባቸውን ቁሳቁሶች ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ፖሊስ በወረዳ 3 አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሀሰተኛ ሰነድ በሚዘጋጅበት መኖሪያ ቤት ውስጥ በህግ አግባብ ባደረገው ብርበራ 13 ሀሰተኛ የመኪና ሊብሬ፣ 10 ሀሰተኛ የቤት ካርታ፣ 2 ሀሰተኛ የጋብቻ ሰርተፍኬት፣ 18 የእጅ በእጅ የሽያጭ ደረሰኞች እና 6 ሀሰተኛ የባንክ ቤት ደረሰኞች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ የዲግሪ፣ የዲፕሎማ እና የስምንተኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ፣ የፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ሀሰተኛ የስራ ልምድ እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ሀሰተኛ አርማዎች (ሎጎ) መገኘታቸውን የጌጃ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ኮማንደር በልሁ ክፍሌ ገልፀዋል።

ሀሰተኛ ሰነድ በሀገር ላይ የሚስከትለውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳት  በመረዳት ሀሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን አበርክቶ ሊወጣ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top