ዋሊያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 2ኛ የምድብ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

11 Mons Ago 261
ዋሊያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 2ኛ የምድብ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

የኢትዮጵያ ወንዶች እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 2ኛ የምድብ ጨዋታውን ከቡርኪና ፋሶ አቻው ጋር ዛሬ ያደርጋል።

በካዛብላንካ ሞላይ ረሺድ ስታዲየም ልምምዱን ሲያከናውን የቆየው ብሔራዊ ቡድኑ፤ ለጨዋታው የመጨረሻ ልምምዱን ትናንት አድርጓል።

ሁለቱ ቡድኖች ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በአል-አብዲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ጃሚህ ለሚን ከጋምቢያ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንደሚመሩት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top