ተጠባቂው የ2023 የባሎን ደ’ኦር ሽልማት ዛሬ ማታ ይካሄዳል - ዘንድሮ ክብሩን የሚጎናፀፈው ማን ይሆን?

12 Mons Ago 391
ተጠባቂው የ2023 የባሎን ደ’ኦር ሽልማት ዛሬ ማታ ይካሄዳል - ዘንድሮ ክብሩን የሚጎናፀፈው ማን ይሆን?

ተጠባቂው የ2023 የባላንዶር ሽልማት ዛሬ ማታ 2 ሰዓት ከ45 ላይ በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ይካሄዳል፡፡

በስነ-ስርዓቱም ላይ በወንዶችና በሴቶች የዓመቱ አሸናፊን ጨምሮ ከ21 አመት በታች (ኮፓ ትሮፊ) ፣ የአመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ (ያሲን ትሮፊ)፣ ጄርድ ሙለር አዋርድ (የአመቱ ምርጥ አጥቂ) እና የአመቱ ምርጥ ክለብ ምርጫ አሸናፊ ይፋ ይደረጋል፡፡

የባላንዶር ሽልማት ጅማሪዉን ያደረገዉ በፈረንሳይ ፉትቦል በተሰኘ መጽሄት በስፖርቱ ዉስጥ እጅግ የተከበረ የግለሰብ እዉቅና ተደርጎ የሚወሰድ አመታዊ ሽልማት በመሆን ነበር፡፡

የመጀመርያዉ የባላዶንር ሽልማት እ.ኤ.አ በ1956 ነበር የተደረገዉ፡፡

እንግሊዚያዊዉ ስታንሊ ማቲዉ ሽልማቱን ለመጀመርያ ጊዜ ያገኘ እግር ኳስ ተጫዋች ነበር፡፡ 

በእግር ኳስ ስፖርት ታሪክ ስማቸዉ በጉልህ ከሚጠቀሱ ተጫዋቾች  መካከል የላንቺሻየሩ ክለብ የብላክ ፑሉ ተጫዋች ስታንሊ ማቲዉ ተጠቃሽ ነዉ፡፡

ባለፉት 15 አመታት የባላንዶሩ መድረክ በሁለት የእግርኳስ ጠበብቶች አሸብሮቆ የነበረ ሲሆን፤ አርጀንቲናዊዉ ኮከብ ሊዮኔል እንድሬ ሜሲ እና ፖርቹጋላዊዉ ኮከብ ክርስትያኖ ሮናልዶ በተለያዩ ጊዜያት 12 የባላንዶር ሽልማቶችን ማንሳት ችለዋል፡፡

ሊዮኔል ሜሲ 7 ጊዜ የባላንዶርን ክብር ሲቀናጅ፤ ክርሲቲያኖ ሮናልዶ 5ቱን በመዉሰድ ይከተለዋል፡፡

በዘንድሮዉ የባላንዶር ሽልማትም ከሃገሩ አርጀንቲና ጋር የአለም ዋንጫን ያሳካዉ አንድሬ ሊዮኔል ሜሲ እና በማንችስተር ሲቲ ቤት የጎል ማሽን የሚል ቅጽል ስም የወጣለት ከክለቡ ጋር የሶስትዮሽ ዋንጫን ያሳካዉ ኤርሊንግ ሃላንድ ተጠባቂዎች ናቸዉ፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top