ባህር ዳር ከተማ ለካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ማለፍ አልቻለም

1 Yr Ago 597
ባህር ዳር ከተማ ለካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል ማለፍ አልቻለም

በ2023/24 የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ማምሻውን የመልስ ጨዋታውን ያደረገው ባህር ዳር ከተማ፤ በቱኒዚያው ክለብ አፍሪካ 3 ለ 0 ተሸንፎ ወደ ምድብ ድልድሉ ማለፍ ሳይችል ቀርቷል። 

60 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው ሃማዲ አግሬቢ የኦሊምፒክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ ባሴም ስራፊ፣ ኪንግስሌይ ኢዱዎና ሀምዲ ላቢዲ ያስቆጠሯቸው ግቦች ክለብ አፍሪካን አሸናፊ አድርገዋል። 

ውጤቱን ተከትሎ ክለብ አፍሪካ በአጠቃላይ ውጤት ባህር ዳር ከተማን 3 ለ 2 በማሸነፍ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድሉ ማለፋን አረጋግጧል። 

ባህር ዳር ከተማ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሲሳተፍ የዘንድሮው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top