በሦስት ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን የሠላም ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

6 Days Ago 260
በሦስት ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን የሠላም ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በአማራ፣በትግራይ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ተግባራዊ የሚሆን በአውሮፓ ህብረት 2 ሚሊዮን ዩሮ የሚደገፍ የሰላም ግንባታ ፕሮጀክትን ዛሬ በአዲስ አበባ ይፋ አድርጓል።
 
ፕሮጀክቱ ወጣቶች የሠላም ግንባታን ባሕል አድርገው እንዲሰሩ የማብቃትና የተሻለ የግጭት አፈታት አቅም እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል።
 
የሠላም ሚኒስቴር የሠላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ሠላም የሁሉም ዜጋ ጉዳይ በመሆኑ ለዘላቂነቱ የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል።
 
መንግሥት በአንዳንድ የአገሪቷ አካባቢዎች የተከሰቱ የሠላም እጦቶችን ለመቅረፍ በንግግር የመፍታት ቁርጠኛ አቋም በመያዝ ችግሮችን በሠላማዊ መንገድ እየፈታ እንደሚገኝ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
 
ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ በመነጋገር ችግሮችን የመፍታት ነባር እሴቶችን በማጎልበት የሠላም እጦት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች ሠላምን ለመገንባት እየሰራ ያለውን ሥራ አመስግነዋል።
 
ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት የሠላም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top