አውሮፕላን ማረፊያንና ድንበርን በተቀናጀ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

6 Days Ago 151
አውሮፕላን ማረፊያንና ድንበርን በተቀናጀ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ
አውሮፕላን ማረፊያን እና ድንበርን በተቀናጀ መልኩ ለማስተዳደር የሚያስችል ስምምነት በዘጠኝ ተቋማት መካከል ተደርጓል።
 
ስምምነቱን ያደረጉት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንዲሁም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ናቸው።
 
ስምምነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ እና አገልግሎቱን ለማዘመን የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
 
ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ መንገደኞችም የሚኖራቸውን ቆይታ እንዲያራዝሙ፣ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበትን መንገድ ማቅለልና አስተማማኝ ደህንነት እንዲኖር ለማስቻል ስምምነቱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው መገለጹን የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top