ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ የሚገኝ የጤፍ ኩታ ገጠም ሰብልን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸው የግብዓት አቅርቦት መጨመር እና አብሮ የመስራት ባሕል መጠናከር አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ ማስቻሉን መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡
አርሶ አደሩ በሰላም እጦት ውስጥ ሆኖ ያስመዘገበውን ውጤት ለማሳደግ ዘላቂ ሰላም እንደሚያስፈልግ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አሁን ላይ በመንግስት ሕግ የማስከበር ስራ አንጻራዊ ሰላም መገኘቱንም ተናግረዋል፡፡
ይህንን አንፃራዊ ሰላም እስከ ቀበሌ ድረስ ዘላቂ ማድረግ እንደሚቻል መገንዘባቸውንም አክለዋል፡፡
በቀጣይ በመስኖ ልማት ስንዴ እና ሌሎችም ምርቶችን ለማምረት ትልቅ ተነሳሽነት እንዲኖር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአማራ ክልል ከ20 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት የታረሰ ሲሆን በዚህም ከ600 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል፡፡