የኢትዮጵያ መንግስት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የአንኳን ደስ አለዎ መልእክት አስተላለፈ

1 Day Ago 102
የኢትዮጵያ መንግስት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የአንኳን ደስ አለዎ መልእክት አስተላለፈ

የኢትዮጵያ መንግስት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የአንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላልፏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በሶማሊላንድ በተደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት በመሆን በመመረጣቸው በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ስም የአንኳን ደስ አለዎት መልእክት አስተላልፏል፡፡

ተመራጩ ፕሬዝዳንትም ሆነ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቤሂ ላሳዩት አርአያነት ያለው ዲሞክራሲያዊ መንግስትነት ኢትዮጵያ አድናቆት እንዳለትም ሚኒስቴሩ በመግለጫው ጠቅሷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መጪው የሶማሊላንድ አስተዳደር ስኬታማ ጊዜ እንዲገጥመው መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top