የአማራ ክልልን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

15 Hrs Ago 56
የአማራ ክልልን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ምላሽ እና ማብራሪያ በየአማራ ክልልን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ታላላቅ የመንገድ፣የኢንዱስትሪ እንዲሁም የቱሪዝም ልማቶች እየተከናወኑ ስለመሆናቸውም አንስተዋል።

በአማራ ክልል ከየትኛውም መንግስት በላይ አሁን ያለው መንግስት በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመላክተዋል።

በክልሉ በዋና ዋና ከተሞች የኮሪደር ልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸው፤ የፋሲል ቤተ-መንግስት እድሳት ላይ ስለመሆኑም አንስተዋል።

የመገጭ ግድብን 7 ቢሊዩን ብር መድበን ከበርካታ ዓመታት የግንባታ መቋረጥ በኋላ ቀን ከሌት እየገነባን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ነገር ግን በክልሉ ልማት እንዳይከናወን ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች ስለመኖራቸው ጠቅሰው፤ ይህን ተባብረን ማስቆም አለብን ብለዋል።

የአማራ ህዝብ ማን እንደሚሰራለትና ማን እንደሚያወራለት ጠንቅቆ የሚያውቅ ጨዋ ህዝብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤መንግስት ክልሉን የማልማት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top