የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ጫና ለመቀነስ እየተሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

15 Hrs Ago 50
የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ጫና ለመቀነስ እየተሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ጫና ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
 
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፎርሙ እጅ አጠር ዜጎችን የሚጎዳ እንዳይሆን ከፍተኛ የድጎማ በጀት መያዙን አስታውቀዋል፡፡
ከደመወዝ ጭማሪ ጋር የተያያዙ የመረጃ ክፍቶችን በማጥራት ማሻሻያው ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡
 
የዋጋ ግሽበት የዓለም ሀገራትን በተለያየ ደረጃ እየፈተነ እንደሚገኝ የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የማምረት አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
 
መንግሥት እንደ ነዳጅ፣ ማዳበሪያ፣ ዘይት እና መድኃኒት ባሉ ምርቶች ላይ ድጎማ ከማድረግ ባሻገር የገበያ ማረጋጋት ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top