በሚቀጥሉት ዓመታት የኢትዮጵያን ዕዳ ከ10 በመቶ በታች ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የብድር ጫና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ጥቅል ምርት አንጻር ከነበረበት ከ30 ነጥብ 6 በመቶ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡
በሚቀጥሉት ዓመታት ይህን አሃዝ ከ10 በመቶ በታች ለማድረግ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ዓመታት መንግስት ምንም አይነት የንግድ ብድር አለመውሰዱን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተጠቀሰው ጊዜ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮ ቴሌኮምን ሳይጨምር 13 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ መክፈሉን ገልጸዋል፡፡
“ይህም ለትውልዱ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ለማውረስ የምናደርገውን ሥራ የሚያግዝ ነው” ብለዋል፡፡