ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያ የኤክትሮኒክ ግብይት ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮ ቴሌኮም ሰዎችን በስልክ ከማገናኘት አልፎ ኢ-ኮሜርስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲያድግ ከፍተኛ ድርሻ እየተጫወተ ይገኛል“ ብለዋል
ተቋሙ የኤክትሮኒክ ግብይት ላይ በትኩረት በመሥራቱ በሀገሪቱ በሞባይል ስልክ የሚፈጸም የግብይት መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አንስተዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች እያስፋፋው የሚገኘው የ5ጂ ቴክኖሎጂም ለዘርፉ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ጠቁመዋል፡፡
ተቋሙ በቅርቡ ያካሄደው የ10 በመቶ የአክስዮን ሽያጭ የተቋሙን አቅም ይበልጥ እንደሚሳድገውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመላክተዋል፡፡