ኢቢሲ DOTSTREAM አዲሱ ተቋም

3 Days Ago 92
ኢቢሲ DOTSTREAM አዲሱ ተቋም

የኢቢሲን የማኀበራዊ ትስስር ገጾች የሚያስተባብር “ኢቢሲ DOTSTREAM” የሚል ስያሜ የተሰጠው አዲስ ተቋም በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ ይፋ አድርገዋል።

ኢቢሲ DOTSTREAM በዲጂታሉ ዓለም የኢትዮጵያን አዎንታዊ መልክ ለማጉላት በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

ኢቢሲ ወደ ይዘት በሚል እያከናወናቸው ካሉ የሪፎርም ሥራዎች ውስጥ አንዱ በዲጂታል የሚዲያ አማራጮቹ ያለውን ተጽዕኖ ፈጣሪነት ማላቅ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከ20 ሚሊዮን በላይ ተካታዮች ያሉትን የኮርፖሬሽኑን የማኀበራዊ የትስስር ገጾች በማስተሳሰር ፤ የኢትዮጵያን ድምጽ ለዓለም የሚያደርሰው ኢቢሲ DOTSTREAM በቅርቡ ስራ እንደሚጀምርም ገልጸዋል።

ኢቢሲ DOTSTREAM በተቋሙ ቻናሎች የሚተላለፉ ይዘቶችን ለኢንተርኔት ሚዲያ ተጠቃሚዎች ይበልጥ ተስማሚ ሆነው ተደራሽ እንዲሆኑ እንደሚያግዝም አቶ ጌትነት ታደሰ ተናግረዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top