የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

2 Days Ago
የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቱርኪዬ መንግስት አመቻቺነት በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተደረገውን ውይይት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል፡፡
 
የሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ላሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ግልፅና ወዳጅነት የተሞላበት የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት እንደነበር ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስታውቋል።
 
ሚኒስቴሩ፤ በቱርኪዬ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ጋባዥነት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ተገናኝተው መወያየታቸውን ነው የገለጸው።
 
በቱርኪዬ መንግስት አመቻቺነት የተካሄደው የሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ላሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ግልፅና ወዳጅነት የተሞላበት የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት እንደነበር በመግለጫው ተመላክቷል።
 
ሁለቱ ሚኒስትሮች ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት ቁርጠኝነታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ የቱርኪዬ መንግስት ውይይቱን ለማመቻቸት ስለተጫወተው ገንቢ ሚናም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
 
ሁለቱ ሚኒስትሮች መልካም ጉርብትናን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ከግምት በማስገባት መፍትሄዎችን ለማመላከት ያለሙ ምክክሮችን ለመቀጠልም መስማማታቸው ተገልጿል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች የቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምክክሩን አገራቸው ለማስተናገድ የወሰዱትን ተነሳሽነት በማድነቅ ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ለመቀጠል መስማማታቸውም ተመላክቷል።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top