አሁን ላይ አብዛኛውን ግዜ ጥንዶች ልጅ መውለድ ባለመቻላቸው ምክንያት ብቻ ትዳራቸው የሚፈርስበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
እንደ ዘርፉ ባለሙያዎች የመካንነት ችግር በተለያየ ምክንያት መፀነስ ወይም ማርገዝ አለመቻልን የሚያመለከት ቢሆንም የተለያዩ ህክምናዎችን በማግኝት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል።
ይሁንና የመካንነት ችግር የባሰ ደረጃ ላይ ሲገኝ ፈፅሞ የመፀነስ እድል አለመኖር በሰዎች ላይ የሚከሰት ሲሆን፤ ይህ አይነት ችግር የመፈጠር እድሉም በጣም አነሳ እንደሆነ ይነገራል።
መካንነት በአብዛኛው አንድ ዓመት (ወይም ከዚያ በላይ) የጾታዊ ግንኙነት ከተደረገ በኋላ ማርገዝ (መፀነስ) አለመቻል እንደሆነ የህክምና ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡
በአሜሪካ ውስጥ በተጠናው ጥናት ከ15 እስከ 49 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ባለትዳሮች መካከል አንዱ ከ1 ዓመት ሙከራ በኋላ ሊያረግዝ አይችልም፡፡
ወላጆች ለመሆን ተስፋ የሚያደርጉ ባልና ሚስቶች ልጅ ለመፀነስ መቸገር ተስፋ አስቆራጭና ያልተጠበቀ ሊሆንባቸው ይችላል።
በሴቶች ውስጥ ያለው የመራባት ሁኔታ ከእድሜ ጋር በተያያዘ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ ስለሚታወቅ በሴቶች ላይ የመካንነት ተጋላጭነት ከፍ ያለ ነው፡፡
በኢትዮጵያ እንዲሁም በሌሎች አንዳንድ ሀገራት መካንነት የሴቶ ብቻ ችግር ተደርጎ ብዙ ጫናዎች በሴቶ ላይ ቢደረጉም፤ መካንነት በወንዶች ላይም እንደሚከሰት ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
መካንነት በሴቶች እንዴት ሊከሰት ይችላል፦
*የዳሌ ቁስል በሽታ ታሪክ፣
*የታወቀ የማህጸን ወይም ቱባል በሽታ
*የእድሜ መጨመር
*የተለያዩ የወር አበባ መታወክ
*የተዋልዶ አካላት የአካል ጉድለቶች እና የመራቢያ አካላት ቁስሎች
*የሴት ዘር (እንቁላል) የመልቀቅ ችግር፣ የማህጸን ጫፍ ችግሮች
*ከአንድ በላይ የፅንስ መጨንገፍ ታሪክ የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በወንዶች በኩል ለመካንነት የሚዳርጉ ምክንያቶች፦
*የቀዶ ህክምና የሰቆቃ ታሪክ
*ቀደም ብሎ የኬሞቴራፒ ሕክምና መጠቀም
*ከመጠን በላይ መወፈር፣ ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥ ወይም የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነት (ኦፒዮድ ፣ ማሪዋና)
*ለአንዳንድ መድኃኒቶች ወይም ለአንዳንድ የአካባቢ መርዛማ ንጥረ ነገሮች መጋለጥ
*በምርመራ ምክንያት በተደጋጋሚ ለከፍተኛ ሙቀት መጋለጥ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
*የፆታዊ ግንኙነት መዛባት፣ የሆርሞን መዛባት የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የመካንነት ህክምናዎች ምንድን ናቸው
*የመጀመሪያው ለእርግዝና ወሳኝ በሆኑ ወቅቶች ፆታዊ ግንኙነት ማድረግ እንድችሉ ማድረግ ሲሆን ይህም ችግሩ ከምን እንደሆነ ለማወቅ ያግዛል።
*የተለያዩ መድሀኒቶችን በመጠቀም መካንነትን ማከም ይቻላል። ለምሳሌ Clomphene እና Serophene ውጤታማ እንደሆኑ ይነገራል
*የተዘጋ የማህፀን ክፍልን በቀዶ ጥገና በመክፈት እንቁላሏና የዘር ፍሬ በቀላሉ እንድገናኙ በማድረግ ህክምና ሊሰጥ ይችላል
በህክምና እገዛ ብዙ መውለድ ያልቻሉ ጥንዶች ወልደዋል፡፡ መካንነት በተለያዩ የህክምና አይነቶች ሊታገዝ ከተቻለ በቀላሉ ሊታከም እንደሚችል የህክምና ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡
በሜሮን ንብረት