እስራኤልና ሃማስ እስረኞችን መለዋወጥ ጀመሩ

13 Hrs Ago 100
እስራኤልና ሃማስ እስረኞችን መለዋወጥ ጀመሩ
በእስራኤልና ሃማስ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ እስረኞች እየተለቀቁ ነው።
 
ከ15 ወራት ጦርነት በኋላ ሃማስ የመጀመሪያዎቹን 3 እስራኤላውያን ሴቶችን የለቀቀ ሲሆን 90 ፍልስጤማውያንም ከእስራኤል እስር ቤቶች ተፈተዋል።
 
በሃማስና በእስራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በሦስት ዙር የሚተገበር ነው። ስምምነቱን ተከትሎም አንዳንዶች በጋዛ በነጻት መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
 
በመጀመሪያው የተኩስ አቁም ስምምነት ምዕራፍ እስራኤል ወደ 1 ሺህ 900 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ትፈታለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሐማስ ደግሞ 33 ታጋቾችን እንደሚለቅ ይጠበቃል።
 
በራፋህ እና በደቡባዊ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመመለስ ግን ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ነው የሚገለጸው።
 
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ መሰረት በጋዛ ዙሪያ ያሉ 60 በመቶ የሚሆኑት ህንፃዎች በእስራኤል ጥቃት ተጎድተዋል፤ይህም ብዙ ተፈናቃዮች በመጠለያ ውስጥ ሊቆዩ እንደሚችሉ የሚያመላክት ነው ተብሏል።
 
እስራኤል በጋዛ ውስጥ በፈጸመችው ጥቃት ከ 46 ሺህ 870 በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴርን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top