በአሜሪካ ተቋርጦ የነበረው ቲክቶክ ተመለሰ

1 Day Ago 141
በአሜሪካ ተቋርጦ የነበረው ቲክቶክ ተመለሰ

በአሜሪካ ለሰዓታት አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረው የቲክቶክ መተግበሪያ አሁን መልሶ መጀመሩ ታውቋል።

ቲክቶክ አገልግሎቱን የመለሰው ተመራጩ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን በሚቀበሉባት የመጀመርያ ቀን ቲክቶክ የአሜሪካ ይዞታውን በተመለከተ መፍትሄ እስኪያገኝ ድረስ ሳይዘጋ እንዲቆይ እንደሚፈቅዱ ሃሳብ በመስጠታቸው ነው ተብሏል፡፡

ቲክቶክ ለአሜሪካ ገዥ የማይሸጥ ከሆነ መተግበሪያው በሀገሪቱ የሚኖረው የአገልግሎት የመጨረሻ ቀን ዛሬ እንዲሆን ተቀጥሮ የነበረ ሲሆን በዚሁ መሰረትም የቲክቶክ አገልግሎት በመላ ሃገሪቱ ለሰዓታት ቋርጦ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

ነገር ግን ዶናልድ ትራምፕ የህጉን አፈፃፀም ለማዘግየት እና ስምምነት ላይ ለመድረስ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት ቃል ከገቡ በኋላ ቲክቶክ አገልግሎትን ወደነበረበት ለመመለስ በሂደት ላይ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም ከ170 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱ እንደተመለሰላቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top