የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

3 Days Ago
የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ መንግስት በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየሰራ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኑሮ ውድነቱ ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለማቃለል መንግስት በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሸ እና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ መንግስት የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ረገድ በተለይም የሌማት ትሩፋት ምርሃ ግብር የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

መንግስት የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ባከናወናቸው ስራዎች የዋጋ ንረቱ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቀ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

የኑሮ ውድነት የበርካታ ሀገራት ጭንቀትና ፈተና መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአንዳንድ ሀገራት ከ60 በመቶ በላይ የደረሰ የዋጋ ንረት እየተመዘገበ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የኑሮ ወድነትን ለመቀነስ ልማቱን መግታት ጊዜያዊ መፍትሔ ቢመስልም በዘላቂነት የሚፈጥረው ቀውስ ግን ቀላል ስላልሆነ ከዋጋ ግሽበት ጋር እየታገልን ፕሮጀክቶችን እየፈጸምን እንገኛለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በብዙ ሀገራት እያጋጠመ ያለው ይህ ችግር በኢትዮጵያም እጋጠመ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ፤ ለዚህም መንግስት የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ በርካታ ኢንሼቲቮችን ቀርጾ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  

ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው፤ ምርታማነት ሲያድግ ሁሉም ይረጋጋል ለዛም እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከዚህ አኳያ በዚህ ዓመት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ከ100 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ብልጫ ያለው ምርት መሰብሰብ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top