የጨጓራ ህመም

9 Mons Ago 7967
የጨጓራ ህመም

የጨጓራ ሕመም/dyspepsia/ በሆድ የላይኛው መካከለኛ ክፍል የሚከሰት ህመም ወይም ምቾት አለመሰማት ነው፡፡ የጨጓራ ህመም በሆድ እቃ ክፍል ደጋግሞ የሚከሰት የማያቋርጥ ቁርጠት ሲሆን ህመሙ ወደ ጎን አካባቢ ጨምሮ ሊስማ የሚችል ነው።

የጨጓራ ህመም በሽታ መነሻ ምክንያት ከመጠበብ እና ከመጨነቅ የተነሣ በየትኛውም አንጀት ወይም በሆድ እቃ ውስጥ አሲድ በመፈጥር እና አገልግሎት እንዳይሰጥ ጨጓራን እንዲላጥ ያደርገዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከምግብ በኋላ ሆድ ቁርጠት፣ መለብለብ ፣ ደረትን መፋቅ ይጀምራል።

የጨጓራ በሽታ ምልክቶች የማቅለሽለሽ ስሜት፣ የሆድ ህመም፣ የሆድ መነፋት፣ ማስታወክ የምግብ አለመፈጨት፣ ስቅታ(ስርቅታ) የመሳሰሉት እንደሆኑ የህክምና ባለሞያዎች ያስረዳሉ።

አብዛኛውን ጊዜ የጨጓራ ሕመም ከባድ ችግር አይደለም፤ ይሁን እንጂ አንድ ሰው ዕድሜው 50 ዓመት ከሆነ በኋላ ከክብደት መቀነስ፣ ምግብ ለመዋጥ መቸገር፣ ተደጋጋሚ ማስታወክ ወይም ጥቁር/የቡና አተላ/ የመሰለ ሰገራ ይስተዋላል።

 በተጨማሪ የቆየ የጨጓራ ሕመም ችግር ካለበት ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል።

ከጉበት፣ ከሐሞት ከረጢት እና ከጣፊያ ጋር የተያያዙ ሌሎች በሽታዎችም ተመሳሳይ ምልክቶች ሊኖራቸው ይችላል።

የጨጓራ በሽታ መፍትሄ ምንድነው ሚለውን ስንመለከት፣ በመጀመሪያ የጨጓራ ህመማችን ምን ዓይነት ምግቦች ስንመገብ ወይም ምን ዓይነት ተግባሮች ስናደርግ ሊነሳብን እንደሚችል ለይተን ማወቅ ነው።

ካፌይን ያላቸው መጠጦች (ለምሳሌ ቡና፣ ሻይ) አለመጠቀም ሲትሪክ አሲድ ያላቸውን የፍራፍሬ ጭማቆዎች (ለምሳሌ፦ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ ወይን ወዘተ) አለመጠቀም፣ ሲጋራ የሚያጨሱ ከሆነ ማቆም፣ ከፍተኛ የቅባት/ፋት/ ይዘት ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ ናቸው፡፡ በፋይበር እና ፍላቮኖይድ የበለፀጉ ምግቦች ኤች.ፓይሎሪ የተባለውን የጨጓራ ባክቴሪያ ዕድገት ስለሚገቱ በጣም ጠቃሚ  የሆኑ  ምግቦች ናቸው፤ ከእነዚህ መካከል፦ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጐመን፣ የምግብ ማጣፈጫ ተክል፣ ጦስኝ፣ ሽምብራ እና አንዳንድ የሻይ ዓይነቶች ይጠቀሳሉ።

ህመሙ ከባሰብን እና ልንቋቋመው ካልቻልን በአፋጣኝ ወደ ሐኪም ቤት መሄድ እንዳለብን የሕክምና ባለሞያዎች ያስረዳሉ።

በሜሮን ንብረት


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top