የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ በአዲስ መልክ ሊሰራ ነው

3 Days Ago
የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ በአዲስ መልክ ሊሰራ ነው
የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ በአዲስ መልክ ሊሰራ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
ሚኒስቴሩ ከመስከረም ጀምሮ ከዚህ በፊት የተሰጠው የኮኮብ ደረጃ ስራ ላይ እንደማይውልም ገልጿል።
 
የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፤ ሚኒስቴሩ አሁን በሚያደረገው የዳግም ደረጃ ምዘና ሂደት ውስጥ የማያልፉ ሆቴሎች ከዚህ ቀደም የተሰጣቸው የኮኮብ ደረጃ በሕጉ መሰረት የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ በመሆኑ እንደሚሰረዝ ተናግረዋል፡፡
 
ይህ ዳግም ምደባ በዋናነት ሆቴሎች የሚሰጡትን አገልግሎት ማሻሻል እና የሀገሪቱን የቱሪዝም አገልግሎት ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ ትኩሩቱን ያደረገ መሆኑንም ገልፀዋል::
 
የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የደረጃ ምደባ ደንብ ሆቴሎች በየሦስት ዓመቱ በዳግም የደረጃ ምደባ ሂደት ማለፍ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡
 
በዚህም መሰረት ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ ከተማ እና በክልሎች የሚገኙ ሆቴሎችን የደረጃ ምዘና ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
 
ሚኒስቴሩ ይህንን ለማድረግ የሚያስችለው መመሪያ ላይም ከሆቴል ባለቤቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየቱን በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top