የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የአስተዳደር ርክክብ ተካሄደ

217 Days Ago 1366
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የአስተዳደር ርክክብ ተካሄደ

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የአስተዳደር ርክክብ መርሀ ግብር ተካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ፣ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አብዲ ዘነበ(ዶ/ር)፣ የጅቡቲ ትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ሀሰን ሁመድ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ከቻይናው የሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር ሊዉ ዌሚን ቁልፍ ተረክበዋል።

በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰራው እና ከአየር ብክለት ነፃ የሆነው የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር 752 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው፡፡

የአዲስ አበባ –ጅቡቲ የባቡር መስመር የቻይና መንግስት ባለቤት የሆኑት የቻይና የባቡር መስመር ግሩፕ (CREC) እና የቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን(CCECC) ግንባታው 2005 ዓ.ም ተጀምሮ በ2010 ዓ.ም የግንባታ ሂደቱ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት መብቃቱ ይታወሳል፡፡

በዚህም የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የአስተዳደር ስራ በቻይናው የሲቪል ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ሲመራ ቆይቷል።

በእነዚህ ዓመታት የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር የተደረገ በመሆኑ፤ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር ስራ በኢትዮጵያና ጅቡቲ አማካኝነት እንዲሆን የሚያስችል የአስተዳደር ርክክብ መርሃ ግብር ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት የስድስት ዓመታት ስኬቶችና የወደፊት ተስፋዎችን የተመለከተ ውይይት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top