ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆኖ ተመረጠ

6 Hrs Ago 161
ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆኖ ተመረጠ

በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ለቀጣይ አራት አመት ፌዴሬሽኑን በፕሬዝዳንት ለመምራት ምርጫ ተከናውኗል፡፡

በዚህም ከኦሮሚያ ክልል የተወከለው ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆኖ ተመርጧል፡፡

በተደረገው ምርጫ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን 11 ድምፅ በማግኘት ምርጫውን ሲያሸንፍ፤ አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም 9 እንዲሁም አቶ ያዬህ አዲስ 4 ድምፆችን አግኝተዋል፡፡

በውጤቱም መሰረት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ለቀጣይ አራት አመት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን በመተካት ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ተመርጧል፡፡

ኮማንደር አትሌት ስለሺ በአቴንስ እና ቤጂንግ ኦሎምፒኮች የብር ሜዳሊያዎች አሉት፡፡

በሄልሲንኪ እና ኦሳካ የአለም ሻምፒዮናዎች የብር ሜዳልያዎች ለሃገሩ ያስገኘ ሲሆን፤ በፓሪስ አለም ሻምፒዮናም የነሀስ ሜዳልያ አምጥቷል፡፡

አቡጃ ላይ በተደረገው የአፍሪካ ጨዋታዎች በ10ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ አስገኝቷል፡፡

በሃብታሙ ካሴ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top