የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ "ኢኮዋስ" በኒጀር በማሊ እና በጊኒ ላይ የጣለውን የኢኮኖሚ እገዳ ማንሳቱን አስታውቋል፡፡
ተቋሙ በሀገራቱ ጥሎት ከነበረው ማዕቀብ መካከል የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ማዕቀብን ማንሳቱ የተገለፀው፡፡
በውሳኔው መሰረት በሀገራቱ ላይ ተጥሎ የነበረው የበረራ ዕገዳ፤ የጎረቤት ሀገራት ድንበርን ክፍት ማድረግን ጨምሮ በሀገራቱ ንብረት ላይ ተጥሎ የነበረው ዕገዳ ተነስቷል ተብሏል፡፡
ይሁን እንጂ በወታደራዊ መሪዎች ላይ የተጣለው የፖለቲካ መዕቀብ ግን አልተነሳም ተብሏል፡፡
በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ላይ የሚገኙት የጊኒ፣ የኒጀር እና የማሊ ወታደራዊ አመራሮች ማዕቀብ መጣሉን ተከትሎ ከኢኮዋስ አባልነት እንደሚለቁ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ ከጁንታ መሪዎች ጋር ለመወያየት ፍላጎት አሳይቷል መባሉን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
15 አባላት ያሉት የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ በቡርኪናፋሶ፤ በኒጀር ፤ በማሊ እና በጊኒ ላይ ማዕቀብ መጣሉ ይታወሳል፡፡