የምክክሩ ባለድርሻዎች የትኞቹን አካላት ወክለው ተሳተፉ?

4 Mons Ago 366
የምክክሩ ባለድርሻዎች የትኞቹን አካላት ወክለው ተሳተፉ?

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ባከናወነው የምክክር ምዕራፍ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። 

ለመሆኑ እነዚህ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች የትኞቹን አካላት ወክለው ተሳተፉ? 

  1. የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች
  • ከየወረዳው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወክሉ የተመረጡ ተወካዮች 
  1. የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች
  • በአዲስ አበባ ከተማ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች 
  1. የተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ የተመዘገቡ)
  • የሃይማኖት ተቋማት
  • ሲቪል ማህበራት
  • የአሰሪዎች ማህበራት
  • የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን
  • የመምህራን ማህበር
  • የአካል ጉዳተኞች ማህበራት
  • የሙያ ማህበራት
  • የቀድሞው ሠራዊት ማህበር (ተቀናሽ ሠራዊት ማህበር)
  • የጋዜጠኞች ማህበር
  • የዩኒቨርሲቲ መምህራን (የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት)
  • የንግድ ማህበራት ምክር ቤት
  • የሴቶች እና ወጣቶች ማህበራት 
  1. የመንግሥት ተወካዮች (በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ያለው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ)
  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት
  • የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት ዳኞች
  • የአዲስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች
  • የአዲስ አበባ ከተማ ፓሊስ ኮሚሽን 
  1. የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ተወካዮች
  • በተለያዩ ዘርፎች በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያላቸው፣ አንቱታን ያተረፉ እና ተፅዕኖ መፍጠር የሚችሉ ግለሰቦች 

ምንጭ፦ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top