በሀረሪ ክልል በዘንድሮው ዓመት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ

12 Days Ago
በሀረሪ ክልል በዘንድሮው ዓመት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ

በሀረሪ ክልል በዘንድሮው አመት 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ገለፁ፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር የዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን አስመልክተው እንደገለፁት ዘንድሮው በሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል።

ከሚተከሉ ችግኞች መካከልም ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ የተለያዩ አይነት ፍራፍሬዎች መሆናቸውን ጠቁመው፤ ይህም የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አንፃር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በሚካሄደው በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረትና የአፈርና ውሃ ጥበቃ የሚያሻሽሉ ሌሎች የደን ዛፎች መዘጋጅታቸውን ገልጸዋል።

እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በክልሉ እየተመናመኑ የሚገኙ የፍራፍሬ ችግኞችን እንደሚገኙበትም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ ተጋላጭነትን በሚቀነስና የችግኝ ፅድቀት መጠንን በሚያሳድግ መልኩ የተፋሰስ ልማት ስራ መሰራቱን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የችግኝ ጣቢያዎችም ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር መቻሉንም አንስተዋል።

በክልሉ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከሚተከሉ 2.5 ሚሊየን ችግኞች ውስጥ 70 በመቶው የጥምር ደን ሲሆን 30 በመቶው ደግሞ የደን ዛፍ መሆኑን መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top